Tuesday, 23 September 2008

ሰላም ወንድም እና እህቶች !
የዘር አምባጓሮ የኃይማኖት ንትርክ ወሎ መች ለመደ : ሥሙ ምስክር ነው ፋጤ ገብረማርያም ሙህዬ ከበደ :: ወሎ - ላኮመልዛ - የአሥራ ሁለት አውራጃዎች (ዋግ - ላስታ - ራያ ቆቦ - የጁ - አምባሰል - ዴሴ ዙሪያ - አውሳ - ቃሉ - ቦረና - ወረኢሉ - ዋድላ ደላንታ እና ወረሂመኖ ) ባለቤት ፣ የሙዚቃ ቅኝቶች (ባቲ - አንች ሆዬ አምባሰል እና ትዝታ ) ምንጭ ፣ የታሪካዊ ቦታዎች (ውጫሌ መቅደላ ላል ይበላ ጊሼን ወዘተ ) ሥፍራ ፣ የሙያ እና የቀለም ትምህርት ቤቶች (ወ /ሮ ስሂን ወልዲያ ወዘተ ) ፣ የሙዚቃ የጀግኖች ባለሙያዎች እና ምሁራን መፍለቂያ ፣ እስላም እና ክርስቲያኑ ፣ ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት እና በእኩልነት የሚኖሩበት አገር ነው :: በጥቅሉ ወሎ ገራገሩ ማለት ይቀላል::

አማርኛው የእኔ ትግርኛውም የእኔ :
አፋርኛውም የእኔ ኦሮምኛውም የእኔ :
አገውኛውም የእኔ አርጎብኛውም የእኔ :
ጋፋትኛውም የእኔ ቆንጆዎችም የእኔ :
ክርስትናው የእኔ እስልምናው የእኔ :
ያም እኔ ያም እኔ ያገር ልጅ ወገኔ :
በጣም ያኮራኛል ንፁህ ኢትዮጵያዊ ወሎዬ መሆኔ ::

የወሎን ህዝብ በትምህርት በግብርና በጤና በባህል ታሪካዊ ቦታዎችን በመንከባከብ እና በመሳሰሉት አብይ አንኳር መስኮች ማሳደግ እና ማዳበር የሁላችንም ጥረት ይሆናል :: ሁላችንም በመተባበር ለዚህ ቀና ዓላማ ግብ መድረስ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማበርከት እንችላለን :: ሥለዚህ በዚህ ዐምድ እና መድረክ ቅን ሃሳቦችን መሠንዘር እንችላለን :: በተጨማሪ ፓልቶክ ውስጥ WOLLO ETHIOPIA SOCIAL & CULTURE VALUES በሚለው ክፍል ውስጥ ቅዳሜ እና እሁድ ከ 21:00 CET ጀምሮ መወያዬት ለብቁ ውሳኔ እና ተግባር ጥርጊያ መንገድ መክፈት ይቻላል :: ፓልቶኩ እንደ አመችነቱ በየቀኑ ይከፈታል ::

ብሩህ ለሆነ ዓላማ አብረን እንነሳ




ስኂን ትጣራለች !!


የሰው አስኳል የሰው እንብርት :


የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት ::


ስንት አርግዘሽ ስንት ወለድሽ :


ስንት ዘርተሽ ስንት አበቀልሽ :


ስንት አትርፈሽ ስንት ገደልሽ :


ስንት አጥፍተሽ ስንት ታደግሽ


ስኂን ስኅኗ መቅረዛዊት :


ያንቺ ውላጅ ያንቺ ቁራጭ :


ያንቺ ፍላጭ ያንቺ ቅዳጅ ::


በምድረ አለሙ ተናኝቶ :


ድንቅ ውሎ ዋለ ጎምርቶ :


ይበል ይበል ተሰኝቶ ::


አዎ ስኂን ስኂኗ መቅረዛዊት :


የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት ::


ዝንተ ዓለም ህያው ነው ግብረ ተመክሮሽ :


እንኳን ቅርስ ነው ምግባረ ውሎሽ ::


አንችስ ህያው ነሽ : ማነው ሞትሽ ያለሽ ?


ስኂን ስኂኗ መቅረዛዊት


የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት ::


1985
















ሕብረት ኃይል ነው ::
እህታችሁ ወረኢሉ ከወሎ ገራገሩ

No comments: